ESSS
MENUMENU

የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ጠፈርተኛ ሴት እድትሆን ጥረት እንደሚደረግ ተገለፀ!

የታዳጊ ሴት ተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ለማጎልበት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከ ሲነርጂ ሃበሻ እና ጂ አይ ዜድ ጋር በመተባበር ቴክኖቬሽን ኢትዮጵያ በሚለው ፕሮግራሙ ያዘጋጀዉ አዉደ ጥናት እየተካሄደ ነዉ፡፡ በአውደ ጥናቱ ላይ 18 የሚሆኑ መተግበሪያዎች የቀረቡ ሲሆን አላማ ጥቅም እና የአሰራር ሂደታቸዉ በተማሪዎቹ ተብራርተዋል፡፡ በቴክኖቬሽን ኢትዮጲያ ባለፈዉ አመት 10 የሚሁኑ መተግበሪያዎች በሴት ተማሪዎች እንደተሰሩ በአውደ ጥናቱ ላይ ተነስቷል ፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂ. ጌታሁን መኩርያ ሴት ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ለማስታጠቅና ቴክኖሎጂን የሚያምን፣ የሚረዳና የሚፈጥር ዜጋ ለመፍጠር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል። በስፔስ ሳይንስ ዘርፍ ኢትዮጵያዊያን ጠፈርተኞችን ለማፍራት በሚደረገዉ ጥረት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ጠፈርተኛ ሴት እንድትሆን ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

የመረጃ ምንጭ:- የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር።

Copyright © 2019 Ethiopian Space Science Society. Designed by Techno Bros